ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ የኮናክሪ ወደብን ጎበኙ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጊኒ ረፐብሊክ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኮናክሪ ወደብን ጎበኙ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ ጋር በመሆን ነው ኦቶኖሜ ዴ ኮናክሪ ወደብን የጎበኙት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ትናንት ነበር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሀገሪቱ የገቡት።
በአልአዛር ታደለ