በኮፍያ እና በሴቶች የእጅ ቦርሳ ላይ በፀሀይ ሀይል የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት የቻለው ኢትዮጵያዊ ወጣት
አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደረሰ ቱቻ የተባለው ወጣት በሚለበሱ ነገሮች ላይ ከሚሰበሰብ የፀሀይ ሀይል በአካባቢው ያለውን የአሌክትሪክ ሀይል ችግር ለመቅረፍ ጥረት አድርጓል።
ወጣቱ በሰራው ድንቅ የቴክኖሎጂ ስራ በኮፍያ እና የእጅ ቦርሳ ላይ የፀሀይ ሀይል በመሰብሰብ የኤሌክትሪክ ሀይል ማንጨት ችሏል።
በሚኖርበት አካባቢ እና በገጠራማ አካባቢዎች የሚስተዋለው የመብራት መቆራረጥ እና ሰዎች የሚያጋጥማቸው ችግር ለዚህ ስራ እንዳነሳሳው ለዶቸቬሌ እንግሊዝኛ ተናግሯል።
በዚህም በኮፍያ እና በሴት የእጅ ቦርሳ ላይ የፀሃይ ሃይል በመሰብሰብ ወደ ኤሌክትሪክ ሃይልነት መቀየር መቻሉን አስረድቷል፡፡
ኮፍያው ሚሞሪ ካርድ የሚይዝ፣ ብርሃን የሚሰጥ እና ሬዲዮም የሚሰራ መሆኑንም ዘገባው ያመለክታል።
የሴቶች ቦርሳም የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት የሚችል እንደሆነ ተገልጿል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!