በህገ ወጥ መልኩ ሲዘዋወር የነበረ ከ4 ሺህ 600 በላይ ተተኳሽ የክላሽ ጥይት ተያዘ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህገ ወጥ መልኩ ሲዘዋወር የነበረ ከ4 ሺህ 600 በላይ ተተኳሽ የክላሽ ጥይት ተያዘ፡፡
በትላንትናው ዕለት ከመቐለ ወደ ባህር ዳር ከተማ ሲጓጓዝ ከነበረ አይሱዙ ኤፍኤስአር መካከለኛ የጭነት ተሽከርካሪ በወልደያ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በጉምሩክ ሰራተኞች አማካኝነት በተካሄደ ፍተሻ ብዛቱ 4 ሺህ 615 የሆኑ ተተኳሽ የክላሽ ጥይቶች ተይዘዋል።
ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹን በመደበቅ ለማሳለፍ የሞከሩ አሽከርካሪውን ጨምሮ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ተጨማሪ ማጣራት እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡
በወልደያ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ አንድ ሳምንት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ10 ሺህ 600 በላይ ተተኳሽ የክላሽ ጥይቶች በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ መያዛቸውን ከፅህፈት ቤቱ ያገኘኘው መረጃ ያመለክታል። ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!