የኮምፒውተሮችን ደህንነት ለመጠበቅ ሊዳብሩ የሚገቡ ልምዶች
አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮምፒውተሮች ሁልጊዜ ለተለያዩ አይነት ውስጣዊና ውጫዊ ጥቃቶች የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡
በመሆኑም ሁልጊዜ የሚጠቀምባቸውን ኮምፒውተሮች አጠቃላይ ባህሪ መረዳት፣ በየጊዜው ማሻሻያ ሊደረግባቸው የሚገባና መቀየር ያለባቸውን ስርዓቶች ማወቅ እንዲሁም መረጃዎች እንዳይጠፉ ጥንቃቄ መውሰድ ይገባል፡፡
ከዚህ አንጻርም ጠቃሚ ፋይሎችን መጠባበቂያ መያዝ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ሥርዓት ለደህንነት ሥጋት እንዳይጋለጥ ማሻሻያና ለውጥ ማድረግ አንቲ-ቫይረስ ሶፍትዌሮችን መጠቀም፣ በየጊዜው መተግበሪያዎችን ማሻሻል እና ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ አጠቃላይ የኮምፒውተር ስርዓትን ስካን ማድረግ አጥፊ ሶፍትዌሮችን የሚከላከሉ ፀረ-አጥፊ ሶፍትዌሮችን መጠቀም እና ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ስካን ማድረግ እንዲሁም የተመጠነ የፋይል አስተዳደር መተግበር እና ዲስኮችን በየጊዜው ማፅዳት እንደሚገባ ከኢንፎርሜሽን እና መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!