Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አምስት ወራት 83 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ ገብተዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አምስት ወራት 83 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 4 ሺህ 359 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ወደ ስራ መግባታቸውን በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ አስታወቁ።

ከእነዚህ ውስጥ 3 ሺህ 519 ወደ ባለሀብትነት የተሸጋገሩ አርሶ አደሮች ሲሆኑ 316ቱ ወጣቶች መሆናቸውን ገልፀዋል።

450ዎቹ ሀገር በቀል ባለሀብቶች እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እና 74 የማስፋፊያ ጥያቄ ያቀረቡ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

ለእነዚህ አልሚዎች 35 ሺህ 920 ሄክታር መሬት ተላልፏል ያሉት አቶ አዲሱ ፕሮጀክቶቹ በሙሉ አቅም ወደ ስራ ሲገቡ ለ313 ሺህ 566 ወጣቶች የስራ ዕድል ይፈጥራሉ ብለዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.