Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት አምስት ወራት በጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር ለክልሎች 9 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ተላለፈ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት አምስት ወራት በጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር ለክልሎች 9 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር እንዲተላለፍ መደረጉን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው አስታወቁ።

በዚህም ከሐምሌ 2012 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም ለአሮሚያ ክልል 3 ቢሊየን 433 ሚሊየን 337 ሺህ ብር ፣ ለአማራ ክልል 2 ቢሊየን 151 ሚሊየን 595 ሺህ ብር፣ ለደቡብ ክልል 1 ቢሊየን 602 ሚሊየን 922 ሺህ ብር እና ለሶማሌ ክልል 994 ሚሊየን 330 ሺህ ብር እንደተላለፈላቸው ተጠቁሟል።

እንዲሁም ለትግራይ ክልል 600 ሚሊየን 789 ሺህ ብር፣ ለሲዳማ ክልል 400 ሚሊየን 730 ሺህ ብር፣ ለአፋር ክልል 300 ሚሊየን 888 ሺህ ብር ፣ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ 182 ሚሊየን 322 ሺህ ብር፣ ለጋምቤላ ክልል 132 ሚሊየን 510 ሺህ ብር እና ለሀረሪ ክልል 75 ሚሊየን 725 ሺህ ብር በጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር እንዲከፋፈላቸው መደረጉን ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

ለ22 ዓመታት ሲያገለግል የቆየው የጋራ ገቢዎች ማከፋፈያ ቀመር በፌዴሬሽን ምክር ቤት በመሻሻሉ ምክንያት ባለፉት 5 ወራት ለክልሎቹ የተከፋፈለው በስምንት ቢሊየን 739 ሚሊየን 668 ሺህ ብር ዕድገት አለው ተብሏል፡

በጋራ ገቢ በሶስት የግብር ዓይነቶች ማለትም ከኤክሳይስ ታክስ፣ ከቫትና ከተርን ኦቨር ታክስ ገቢዎች  እደተገኘ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

የሌሎች የታክስ አይነቶች በመሰራት ላይ ሲሆኑ በቀጣይ ተጠቃሎ የሚገለፅ እና የሚላክ ይሆናልም ነው ያሉት፡፡

ሚኒስትሩ የጋራ ገቢው ድርሻ ያደገው የጋራ ገቢ ማከፋፈያ ቀመሩ በመቀየሩ እና የተቋሙ ገቢ የመሰብሰብ አቅም እያደገ በመምጣቱ እንደሆነም ተናግረዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.