Fana: At a Speed of Life!

ቤንያሚን ኔታኒያሁ ላለመከሰስ መብታቸው ዋስትና እንዲሰጣቸው ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ የሀገሪቱ ፓርላማ ላለመከሰስ መብታቸው ዋስትና እንዲሰጣቸው ጠየቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሁለት ዓመታት ምርመራ ሲካሄድባቸዉ ቆይቶ ከወራት በፊት በሙስናና ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም ወንጀል ክስ ተወንጅለዋል።

ኔታንያሁ ለፓርላማው ያለመከሰስ መብት ጥያቄ በማቅረባቸው በመጭው መጋቢት እስከሚካሄደው ምርጫ የክስ ሂደታቸው እንዲዘገይ ያደርጋል ተብሏል።

ከሙስና ጋር በተያያዘ ምንም ወንጀል አልሰራሁም የሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ያመለከሰስ መብታቸው ዋስትና እንዲያገኝ ከምክር ቤቱ ግማሽ ያክል ድምፅ ማግኘት ይኖርባቸዋል ነው የተባለው።

እስራኤልን ለረጅም ዓመታት የመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ከአንድ ባለሀብት ስጦታ ተቀብለዋል እንዲሁም በሚዲያው ላይ ሰፋ ያለ ሽፋን ለማግኘት እንዲችሉም ስልጣናቸውን አላግባብ ተጠቅመዋል በሚል ክስ እንደቀረበባቸውም ይታወሳል።

የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉት ኔታንያሁ የሀገሪቱ ፓርላማ ላለመከሰስ መብታቸው ዋስትና ከሰጠ የክስ ሂደቱ አይጀመርባቸውም።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.