የአንድነት ፓርክ ከዋሻ ግንባታው ጋር ተያይዞ መደበኛ የጉብኝት አገልግሎቱን አያቋርጥም
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአንድነት ፓርክ ከዋሻ ግንባታው ጋር ተያይዞ መደበኛ የጉብኝት አገልግሎቱን እንደማያቋርጥ አስታወቀ።
የአንድነት ፓርክ መደበኛ የጉብኝት አገልግሎት ከሂልተን ሆቴል ተነስቶ ወደ ካዛንችስ በሚታጠፈው እና ከካዛንችስ ወደ 4 ኪሎ የሚያስወጣው መንገድ መዘጋት ምክንያት አይቋረጥም ነው ያለው።
አንድነት ፓርክን ያለ ትራፊክ መጨናነቅ መጎብኘት የሚያስችል የፓርኩን የመኪና ማቆሚያ ከግቢው የሚያገናኝ የውስጥ ለውስጥ ዋሻ ግንባታ በነገው ዕለት እንደሚጀመር መዘገባችን ይታወሳል።
ይሁንና ግንባታው በፓርኩ መደበኛ እንቅስቃሴ ላይ ምንም አይነት ተፅእኖ አንደማይኖረው የተገለፀ ሲሆን፤ የፓርኩ መደበኛ የጉብኝት አገልግሎት የሚቀጥል መሆኑ ተጠቁሟል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!