የጆ ባይደን የምርጫ አሸናፊነት በኤሌክቶራል ኮሌጁ ተረጋጋጠ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጆ ባይደን የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊነታቸው በኤሌክቶራል ኮሌጅ ተረጋግጦላቸው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው በይፋ ተሰየሙ፡፡
የየግዛት ተወካዮቹ ባይደን ወደ ነጩ ቤተ መንግስት መግባት የሚያስችላቸውን ማረጋገጫ የሚያገኙበትን እና ከህዝብ ያገኙትን ውክልና ለተመራጩ ፕሬዚዳንት ሰጥተዋል፡፡
ይህን ተከትሎም የባይደን አሸናፊነት እውቅና ያገኘ ሲሆን፥ ባይደንም በፈረንጆቹ ጥር 20 ቀን ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ፡፡
ባይደን ባደረጉት ንግግር “ የአሜሪካ ዴሞክራሲ ተገፍቶና ስጋት ላይ ወድቆ ነበር” በማለት “እውነተኛ እና ጠንካራ መሆኑን አስመስክሯል” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
በንግግራቸውም ፕሬዚዳንት ትራምፕ የምርጫውን ውጤት ለመቀልበስ ያደረጉትን ጥረት ኮንነዋል፡፡
በአሜሪካ የምርጫ ህግ መሰረት መራጮች በቀጥታ ለዕጩ ፕሬዚዳንቱ ሳይሆን ለግዛት ወኪሎች ድምጽ ይሰጣሉ፡፡
የግዛት ወኪሎችም ከሕዝብ ያገኙትን ውክልና በድምጻቸው በማረጋገጥ ፕሬዚዳንቱን በይፋ ይመርጣሉ፡፡
በኤሌክቶራል ኮሌጁ የሚሰጠው ማረጋገጫ ባይደን ወደ ኋይት ሃውስ እንዲገቡ የሚያስችል የመጨረሻው ማረጋገጫ የድምጽ አሰጣጥ ስነ ስርአት ነው፡፡
በተደጋጋሚ የምርጫውን ውጤት አልቀበልም ሲሉ የቆዩት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስካሁን ያሉት ነገር የለም፡፡
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!