በትግራይ ክልል የተካሄደው ህግን የማስከበር ስራ ተጠናቋል – አምባሳደር ዶ/ር ትዝታ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መንግስት በትግራይ ክልል የወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ በስኬት መጠናቀቁን በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ትዝታ ሙሉጌታ ገለፁ።
አምባሳደሯ ዩናይትድ ኒውስ ኦፍ ኢንዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ህግ የማስከበር እርምጃው ተጠናቆ ዜጎችን መልሶ ወደ ማቋቋም ስራ መገባቱን ተናግረዋል።
ቀሪው ስራም የተደበቁ የህወሓት ቡድን አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋልና ለህግ ማቅረብ ነው ብለዋል፡፡
ህግን የማስከበር እርምጃው ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ሁሉንም ዓላማዎች በስኬት ማጠናቀቅ ተችሏልም ነው ያሉት፡፡
የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ከማቋቋም ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያ መንግስት ጥሩ ልምድ እንዳለውም አስረድተዋል።
በመሆኑም ቀጣይ የመንግስት ስራ ወደ ሱዳን የተሰደዱ እና በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎችን ማቋቋም እንደሆነም ገልፀዋል፡፡