በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጭሮ ወረዳ በተፈጠረ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጭሮ ወረዳ በተፈጠረ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ።
አደጋው የተከሰተው በወረዳው ያብዶ ቦባሳ ቀበሌ በተለምዶ ኮሎሎ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ነው።
የምዕራብ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ ጽ/ቤት እንደገለጸው አደጋው ያጋጠመው ከአዳማ ከተማ ወደ ጭሮ ሲጓዝ የነበረ ቦቴ ከህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው።
በአደጋው ህይወታቸውን ካጡት 8 ሰዎች በተጨማሪ፣ 19 ሰዎች ላይ ጽኑ ጉዳት፣ 10 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ይገኛል ተብሏል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!