የብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ተወካዮች በአዲስ አበባ በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተለያዩ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ተወካዮች በአዲስ አባባ ከተማ በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በመስቀል አደባባይ በመገኘት ለብሔር፣ ብሔረሰቦች ተወካዮች በከተማዋ ግንባታቸው የተጠናቀቁ እና በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል ።
አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ከተማ ናት ያሉት ወይዘሮ አዳነች ከተማዋን ለኑሮ ምቹ እና ለጎብኚዎች መዳረሻ ለማድረግ በርካታ ፕሮጀክቶች መሰራታቸውን እና በመሰራት ላይ እንዳሉ አስረድተዋል።
የሸገር ማስዋብ ፕሮጀክት የወዳጅነት ፓርክ ፣ የእንጦጦ ፓርክ ፣ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት፣ የአድዋ ዜሮ ኪሎ ሜትር እና የሸገር ዳቦ እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን በስክሪን ታግዘው ለተወካዮቹ ገለጻ አድርገውላቸዋል።
ተወካዮቹ የአንድነት ፓርክን ጨምሮ የወዳጅነት ፓርክ እና የእንጦጦ ፓርክን እንደሚጎበኙ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!