ስፖርት ለአንድነት እና ለሰላም መፍትሄ ነው- ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ስፖርት ለአንድነት እና ለሰላም አይነተኛ መፍትሄ መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።
የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር (አኖካ) ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ አካሄዷል።
በጉባኤውም ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ፕሬዚዳንት ሙስጠፋ ቤራፍ እና የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ተገኝተዋል።
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በመክፍቻ ንግግራቸው ኢትዮጵያ ብሔራዊና አህጉራዊ ግቦችን ለማሳካት ወሳኝ ሚና እንደምትጫወት ገልጸዋል።
አያይዘውም የጋራ ዓላማን ለማሳካት ስፖርት ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።
ለዘርፉ ስኬት ሁሉም የተቻለውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!