Fana: At a Speed of Life!

ቻይና በባይደን ቡድን ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር እየጣረች መሆኑ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቻይና በቅርቡ ስልጣናቸውን በሚረከቡት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር እየጣረች መሆኑን የአሜሪካ የደህንነት ባለስልጣናት አስታወቁ፡፡

በሀገሪቱ ብሔራዊ የደህንነት ተቋም ውስጥ ባልደረባ የሆኑት ዊሊያም ኢቫኒና እንደገለጹት ቻይና በባይደን ቡድን ውስጥ የሚሰሩ ግለሰቦችን ኢላማ ማድረጓን ነው የገለጹት፡፡

ኢቫኒና በባይደን ቡድን ላይ የተደረገው ተጽዕኖ የተጠናከረ ነበር ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ቻይና አሜሪካ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ለማግኘት በምታደርገው ጥረት እና በቅርቡ በተካሄደው ምርጫ ጣልቃ ለመግባት መሞከሯን ነው ያስረዱት፡፡

ኢቫኒቫ ቀጣዩ አስተዳደር ይህንን የቻይና ተፅዕኖ መረዳት መቻል አለበትም ነው ያሉት፡፡

2020 በተደረገው የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ትራምፕ ቻይና ባላቸው የባንክ ደብተር እንዲሁም ባይደን ልጃቸው ሃተር ከቻይና ጋር ባካሄደው የንግድ ስምምነት ዙሪያ ስማቸው ሲነሳ እንደነበር ይታወሳል፡፡

 

ምጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.