ጠ/ሚ ዐቢይ በትግራይ ክልል የተካሄደው ህግን የማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁን አስታወቁ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትግራይ ክልል የተካሄደው የህግ ማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁን አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፥ “በትግራይ ክልል ስናካሂድ የነበረው የህግ የማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁን እና መቆሙን ላሳውቅ እወዳለሁ” ብለዋል።
“ቀጣይ ትኩረታችንም ክልሉን መልሶ መገንባት እና ሰብአዊ ድጋፎችን መድረስ ነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
በዚሁ ጊዜም የፌደራል ፖሊስ በህግ የሚፈለጉ ወንጀለኛ የህወሓት አባላትን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እንደሚሰራም ገልፀዋል።