Fana: At a Speed of Life!

በአውስትራሊያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች  ከሰደድ እሳት ለማምለጥ ወደ ባህር ዳርቻዎች ተሰደዋል

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 21፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውስትራሊያ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከሰደድ እሳት ለማምለጥ ወደ ባህር ዳርቻዎች እየተሰደዱ ነው፡፡

በአካባቢው ባለው  ከፍተኛ ሙቀት እና ንፋስ በአውስትራሊያ የተከሰተው ሰደድ እሳት ወደ ተለያዩ ግዛቶች እየተስፋፋ መሆኑ ነው የተገፀው፡፡

እሳቱ ወደ የቪክቶሪያ የባህር ዳርቻ ከተማ ወደ ሆነችው ማላኮታ የተዛመተ ሲሆን  የአካባቢው ነዋሪዎች በውሃ ዳርቻዎች ላይ መጠለልና ጀልባዎች ላይ ተሳፍሮ መቆየት ግድ ሆኖባቸዋል ነው የተባለው፡፡

ነዋሪዎቹም ደም በለበሰው ሰማይ ሥር ተጠልሎ መቆየት በጣም  ፈታኝ እንደሆነባቸው ተናግረዋል፡፡

በሲድኒና ሜልቦርን መካከል በርካታ በዓል ወደ ሚከበርባቸው ቦታዎች የሚወስዱ መንገዶች በሰደድ እሳቱ ምክንያት መቋረጠቻው ተገልጿል፡፡።

እየተስፋፋ በመጣው ሰደድ እሳት ሰዎች ለህልፈት እየተዳረጉ ሲሆን ገሚሶቹም የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል፡፡

ጎብኝዎች እና በአካባቢው ያሉ ሰዎች አሁን አካባቢውን ለቆ ለመውጣት ስለረፈደ እንዲሁም አደገኛ በመሆኑ ባሉበት እንዲቆዩ የአካባቢው ባለስልጣናት አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.