መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት እጅ እየሰጡ ነው
አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መንግሥት የሰጠውን የ72 ሰዓት ጊዜ በመጠቀም እጅግ በርካታ የትግራይ ሚሊሻና ልዩ ኃይል አባላት በየግንባሩ እጅ እየሰጡ መሆኑን የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
በአፋር ክልል በኩል ብዙዎች ገብተው እጅ የሰጡ ሲሆን በማይ ጸብሪ ተቆርጦ የቀረው ኃይል እጁን በሰላም በመስጠት ላይ መሆኑንም ጠቅሷል።
ጥሪውን ሰምተው እጅ በመስጠት ላይ ለሚገኙ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ አባላት ለሕዝባቸውበማሰባቸው መንግሥት ምስጋናውን ያቀርባልም ብሏል።
“በጁንታው ኃይል ተጽዕኖ ውስጥ ሆናችሁ እጅ ለመስጠት ያልቻላችሁ ሁሉ፣ በያላችሁበት ትጥቃችሁን ፈትታችሁና የጁንታው መጠቀሚያ ከመሆን ተቆጥባችሁ፣ መከላከያ እስከሚደርስላችሁ እንድትጠብቁ በአጽንዖት እናሳስባለን” ብሏል የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ማጣሪያ ባወጣው መረጃ።