Fana: At a Speed of Life!

በትራንስፖርት ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የተመራው ልዑክ ከሱዳን የመሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚንስትር ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢፌዴሪ ትራንስፖርት ሚንስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ ከሱዳን የመሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚንስትር ሀሺም ጣሂር ሼክ ጣሃ ጋር ተወያየ።

በትራንስፖርት ሚንስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የተመራውና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ካሳለፍነው እሁድ ጀምሮ በሱዳን ካርቱም ጉብኝት እያካሄደ ይገኛል።

በትናንትናው እለትም ልዑኩ ከሱዳን የመሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚንስትር ሀሺም ጣሂር ሼክ ጣሃ ጋር  ተገናኝተው መወያየታቸውን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና ሱዳንን በትራንስፖርት ለማስተሰር እንዲሁም በወደብ አጠቃቀም እና በዘርፉ የተደረጉ ስምምነቶችን ለመተግበር በተካሄዱ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ዙሪያ መክረዋል።

በምክክሩ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ፖርት ሱዳንን ስትጠቀም ያጋጠሙ ማነቆዎችን በጋራ መፍታት እንዲሁም በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ አካባቢዎች ፖርት ሱዳንን በመጠቀም የወጪ-ገቢ ንግድን ለማሳለጥና ማዳበሪያን ጨምሮ ሌሎች ምርቶችን በዚሁ ወደብ በመጠቀም ለማስገባት የሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ከመሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚንስትር እንዲሁም ተጠሪ ከሆኑ መስሪያ ቤቶች መካከል የሱዳን የባህር ወደብ ባለስልጣን፣ ከሱዳን ምድር ባቡር፣ ከሱዳን መንገዶች ባለስልጣን ኃላፊዎች ጋር በኮሪደሩ የተሰሩና በሂደት ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ያሉበትን ደረጃ በተመለከተ ውይይት ተካሂዷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.