Fana: At a Speed of Life!

መሰረተ ልማትን በማውደም እየሸሸ የሚገኘው የህወሃት ጁንታ የአክሱም አየር ማረፊያ ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)መሰረተ ልማትን በማውደም እየሸሸ የሚገኘው የህወሃት ጁንታ የአክሱም አየር ማረፊያ ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለጸ።
የኢዜአ ምንጮች እንደገለጹት፤ ቡድኑ በመሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ውድመት እየፈጸመ በመሸሽ ላይ ይገኛል።
በዚህ ድርጊቱም ዘርፈ ብዙ ጥቅም እየሰጠ ይገኝ በነበረው የአክሱም አየር ማረፊያ ላይ ጉዳት ደርሷል።
የቱሪስት መዳረሻ በሆነችው የአክሱም ከተማ የተገነባው የአየር ማረፊያ በ526 ሚሊየን 860 ሺህ 200 ብር ወጪ የተገነባ መሆኑን የኢዜአ ዘገባ ያመላከተ ሲሆን ለአካባቢው ማህበረሰብና ለአገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ሰፊ ነበር።
የአየር ማረፊያው መጎዳት የአክሱም ሐውልትን ከጉዳት ለመታደግ የሚደረገውን የጥገና ስራ ማስተጓጎልን ጨምሮ በርካታ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል ተጠቁሟል።
በቱሪስቶች ዘንድ የሚያወቀው ይህ አየር ማረፊያ በቀንና በምሽት አገልግሎት የሚሰጥና የተሟላ እንደነበር መረጃው ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.