በኪስማዮ ሴክተር ስድስት የተሰማራው የ5ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኪስማዮ ሴክተር ስድስት የተሰማራው የ5ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አመራሮችና አባላት የተቃጣብንን የክህደት ጥቃት አክሽፈን ለህዝባችን ህግ እናስከብራለን በሚል ርዕስ ውይይት አካሂደዋል ።
ውይይቱን የመሩት የሻለቃው ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሌ/ኮ አሰፋ መኮነንን ናቸው።
በወቅቱም አረመኔው የጁንታው ቡድን ከውልደቱ እስከ አሁን ድረስ በሴራ የተሞላ ፣ ለስልጣንና ለገንዘብ ሲል የሚቃወመውን ሲያስር ፣ ሲገርፍ ፣ ሲያሳድድና ሲገድል የኖረ እንዲሁም የሃገሪቱን ሃብትና ንብረት ሙልጭ አድርጎ የመዘበረ ቡድን ነው ብለዋል፡፡
ይህ ሁሉ ድርጊቱ አልበቃው ብሎ በሰሜን ዕዝ ሰራዊት ላይ ዘግናኝ ግፍ ፣ ብሎም በሃገራችን ሉዓላዊነት ላይ የተቃጣ የመጨረሻ የአረመኔነት ጥግ ሲሉም አውግዘዋል ፡፡
ሰራዊቱ በዚህ እኩይ ተግባር ሳይዘናጋ በተሰማራበት ግዳጅ የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባልም ነው ያሉት ፡፡
ከውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ፣ ሰራዊቱ በተኛበት የተደረገው ዘግናኝ ድርጊት በጣም የሚያሳፍር ነው ሲሉ አውግዘውታል፡፡
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።