ቻይና ለክረምት ኦሎምፒክ ፈጣን ባቡር ክፍት ልታደርግ ነው
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2012(ኤፍቢሲ) ቻይና በዋና ከተማዋ ቤጂንግ እና በሀቤይ ግዛት ዘሃንግጃኩ መካከል የተዘረጋውን ፈጣን ባቡር ለገልግሎት ክፍት ልታደርግ መሆኑ ተሰምቷል።
ቻይና የፈጣን ባቡሩን ለአገልግሎት ክፍት የምታደርገው በአውሮፓውያኑ 2022 የምታስተናግደውን የክረምት ኦሎምፒክ ምክንያት በማድረግ እንደሆነም ተነግሯል።
ፈጣኑ ባቡር በሰዓት 350 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ሲሆን፥ በዓለማችን ላይ የመጀመሪያው አሽከርካሪ አልባ ባቡር እንደሚሆንም ተነግሮለታል።
የ 174 ኪሎ ሜትር ያለው የባቡር መስመር ዝርጋታ ፕሮጀክቱ ለ2022 የክረምት ኦሎምፒክ እና የፓራሎምፒክ ታስቦ የተሰራ መሆኑም ታውቋል።
የባቡር መስመሩ የክረምት ኦሎምፒኩን በሚያስተናግዱት በሁለቱ ከተሞች መካከል የነበረውን የ3 ሰዓት መንገድ ወደ 47 ደቂቃ የሚቀንስ መሆኑ የቻይና ባቡር ኮርፖሬሽን አስታውቋል።
ምንጭ፦ newsus.cgtn.com