የተማሪዎች የፈጠራ ስራ ውድድር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 1 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር ከስቲም ፓወር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የተማሪዎች የፈጠራ ስራ ውድድር እየተካሄደ ነው።
“የዓለም የሳይንስ ቀን ለሰላም እና ለእድገት” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው በዚህ ውድድር በአጠቃላይ የትምህርት ዘርፉ ውስጥ ከተለያየ ቦታ የተውጣጡ የፈጠራ ባለሙያዎች ስራቸውን አቅርበዋል።
የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ገረመው ሁሉቃ ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ካሪኩለሙን በማሻሻል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የመማር ማስተማር ሂደቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ለማድረግም ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡
በዝግጅቱ ላይ በፈጠራ ስራ ዙሪያ የፓናል ውይይት እና የፈጠራ ስራዎች አውደ ርዕይ መካሄዱም ነው የተገለጸው።
የውድድሩ ዓላማ የሳይንስ እና የፈጠራ ስራን በአጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ ውስጥ ለማበረታታት እና ተማሪዎች የፈጠራ ስራዎቻቸውን እንዲያወጡ ለማስቻል መሆኑም በዝግጅቱ ላይ ተገልጿል።
የዓለም የሳይንስ ቀን በኢትዮጵያ ለአምስተኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ 18ኛ ጊዜ በትምህርት ሚኒስቴር እና በስቲም ፖወር አዘጋጅነት እየተከበረ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።