አቶ ቢኒያም ምሩፅ ይፍጠር የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ቢኒያም ምሩፅ ይፍጠር የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል።
የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በትናነትናው እለት ፌዴሬሽኑን ለ4 ዓመታት የሚመራውን የፕሬዚዳንት ምርጫ ማካሄዱን የአዲስ አበባ ሰፖርት ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል።
በፌዴሬሽኑ በፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር 4 ዕጩዎች ቀርበው የነበሩ ሲሆን፥ የአንጋፋው አትሌት ምሩፅ ይፍጠር ልጅ የሆኑት አቶ ቢኒያም ምሩፅ በምርጫው አሸናፊ መሆን ችሏል።
ይህንን ተከትሎም አቶ ቢኒያም ምሩፅ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ለቀጣይ 4 ዐመታት ከስራ አስፈፃሚ አባላቶቻቸው ጋር በፕሬዚዳንት የሚመሩ ይሆናል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አትሌቲክስ_ፌዴሬሽን አዲሱ ፕሬዝዳንት አቶ ቢኒያም ምሩፅ ይፍጠር ከቀድሞ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ከአቶ ብርሀኑ መኮንን ጋር የሰነድ እርክክብም አደርገዋል።
በዚሁ ወቅትም አቶ ቢኒያም ምሩፅ ባደረጉት ንግግር፥ “አባቴን ኢትዮጵያዊ የሩጫ ታሪክ እኔ በአመራርነት እና በሀላፊነት እንድወጣው ሁላችሁም ከጎኔ እንድትሆኑ በአክብሮት እጠይቃለሁ” ብለዋል።
በቆይታችን መልካም ተግባር በማከናወን በአትሌቲክሱ በአዲስ አበባ ከተማ ውጤታማ ስራ ለመስራት ከስራ አስፈፃሚ አባላት ጋር በመሆን የተጣለባቸውን አደራ ለመተግባር ቃል እንደሚገቡም አረጋግጠዋል።