በቻምፒየንስ ሊጉ ባርሴሎና ጁቬንቱስን ከሜዳው ውጭ አሸንፎታል
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ምሽቱን ተካሄደዋል።
ከምድብ አምስት እስከ ስምንት ባሉት ቡድኖች መካከል በተካሄደ ጨዋታ ታላላቆቹ ቡድኖች ድል ቀንቷቸዋል።
በምድብ አምስት የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ከሜዳው ውጭ ክራስኖዳርን 4 ለ 0 እንዲሁም ሲቪያ ሬኔስን 1 ለ 0 አሸንፈዋል።
በምድብ ስድስት ቦሩሲያ ዶርትመንድን ዜኒትን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ ክለብ ብሩጅ ከላዚዮ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ አንድ አቻ ተጠናቋል።
ተጠባቂው ጨዋታ በምድብ ሰባት ጁቬንቱስን ከባርሴሎና አገናኝቷል።
ጨዋታውን ባርሴሎና 2 ለ 0 ሲያሸንፍ ደምበሌ እና ሜሲ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
የሃንጋሪው ኤፍ ቲ ሲ ከዳይናሞ ኬቭ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ፍጸሜውን አግኝቷል።
በምድብ ስምንት ደግሞ ማንቼስተር ዩናይትድ አር ፒ ሌፕዚግን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት መርታት ችሏል።
በምድቡ ሌላኛ ጨዋታ ከሜዳው ውጭ የተጫወተው ፒ ኤስ ጂ ኢስታንቡል ባሻክሼርን 2 ለ 0 አሸንፎ ተመልሷል።