ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የእምቦጭ አረምን የመከላከል ዘመቻ ይካሄዳል
የጣናን ህልውና መታደግ ለአማራ ክልል ብቻ የሚተው ሳይሆን ሁሉም ክልሎች እንዲሳተፉ የፌደራል መንግስት መወሰኑን አስረድተዋል።
በአንድ ወር ለሚከናወነው የዘመቻ ሥራ በቀን ከ250 እስከ 300 ሰው በቀበሌ ደረጃ እንደሚሠማራና የሚያስተባብር የክልል እና የፌደራል አካላት የተካተቱበት ኮሚቴ እንደተቋቋመም አቶ ግዛቸው ገልጸዋል።
እምቦጭ በተከሰባቸው 30 ቀበሌዎች ሁሉም ክልሎች ተከፋፍለው እንደሚሰሩትም ነው ዳይሬክተሩ የተናገሩት።
በናትናኤል ጥጋቡ