በፈረንሳይ ውሾች ኮሮና ቫይረስ ያለባቸውን ሰዎች በማሽተት እንዲለዩ ስልጠና እየተሰጣቸው ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ ኮርሲካ የሚገኙ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ውሾች ኮሮና ቫይረስ ያለባቸውን ሰዎች በማሽተት እንዲለዩ የሚያስችል ስልጠና እየሰጧቸው ነው፡፡
ስልጠናው ውሾቹ የሰዎቹን የሰውነት ጠረን በማሽተት በኮሮና ቫይረስ መያዝ አለመያዛቸውን ለመለየት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
ውሾች በተፈጥሯቸው ካንሰርን ጨምሮ ሌሎች በሽታዎችን የመለየት ችሎታ እንዳላቸው ይነገራል፡፡
ከዚህ አንጻርም የሰውነትን ጠረን በማሽተት ቫይረሱ ያለባቸውን እና የሌለባቸውን ሰዎች መለየት እንደሚችሉም ታምኖባቸዋል፡፡
ይሀን መሰሉ ሙከራ ከዚህ ቀደም በታላቋ ብሪታንያ እና አሜሪካ የተሞከረ ሲሆን፥ የአሁኑ ስልጠናም ውሾቹ እንደ አውሮፕላን ማረፊያዎች ባሉና ሰው በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ የመለየት ስራ እንዲሰሩ ያስችላቸዋል ነው የተባለው፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ