ሩሲያ ከመስመር ዝርጋታ ውጭ የሆነ የበይነ መረብ አገልግሎትን ሙከራ አካሄደች
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)ሩሲያ ለአለም አቀፍ በይነመረብ አማራጭ የሚሆን አር ዩ ኔት የተሰኘ ኢንተርኔት በተሳካ ሁኔታ መሞከሯን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል ፡፡
ይሁን እንጂ የተከናወነውን ሙከራ በተመለከተ ዝርዝር መረጃ አለመሰጠቱ በዘገባው ተመላክቷል።
እንደ ሀገሪቱ ኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር መረጃ ፥ማንኛውም ተጠቃሚ በተደረገው ሙከራ ወቅት ምንም አይነት ለውጥ ማስተዋል አለመቻሉን አስታውቋል፡፡
የሙከራ ውጤቱም ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ይቀርባል ነው የተባለው ፡፡
ምሁራኖችበ አንዳንድ ሀገሮች በበይነ መረብ የሚደርስ ጥፋትን እንዳለ ይጠቅሳሉ።
በጥናቱ ዩኒቨርሲቲ የኮምፒተር ሳይንቲስት የሆኑት ፕሮፌሰር አላን ውድዋርድ እንዳሉት፥ በሚያሳዝን ሁኔታ የበይነመረብ ሰርጎ ገቦች መበራከት የሩሲያ የጉዞ አቅጣጫ ሌላ ደረጃ እያደረሰ ነው።
ቁጥራቸው እየጨመረ ያሉ ሃያላን መንግስታት ዜጎች የሚያዩትን መቆጣጠር የሚፈልጉ ስለመሆናቸው ከኢራን እና ከቻይና መመልከት ይቻላል።
ይህ ማለት ሰዎች ሀገራቸው ውስጥ ስለሚሆነው ነገር የመነጋገር እድል አይኖራቸውም፡፡
የተገኘው ውጤት እንደሚያሳየው ባለስልጣኖች እና የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ውጤታማ ምላሽ በመስጠት አደጋዎች እና ስጋቶችን ማስወገድ እንዲሁም በሁለቱም በይነመረብ እና ቴሌኮሙዩኒኬሽን አውታር መረብ ውስጥ የተስተካከለ አሠራር በሩሲያ ፌዴሬሽን እንዲኖር ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸው ተነግሯል።