Fana: At a Speed of Life!

በጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ግድያ ከተከሰሱት ሰዎች መካከል 5ቱ የሞት ፍርድ ተፈረደባቸው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የሪያድ የወንጀለኛ ፍርድቤት ከጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ግድያ ጋር ተያይዞ ከተከሰሱት ሰዎች መካከል 5ቱ ላይ የሞት ፍርድ ውሳኔ አሳልፏል።

የሳዑዲ አረቢያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በዛሬው እለት እንዳስታወቀው፥ ባሳለፍነው ዓመት ጥቅምት ወር ላይ በቱርክ ኢስታንቡል ውስጥ ከተገደለው ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ጋር ተያይዞ በአምስት ሰዎች የሞት ቅጣት ተፈርዷል።

ሆኖም ግን አሁንም ሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑንም አስታውቋል።

አቃቤ ህጉ ሻላን አል ሻላን በሰጡት መግለጫ፥ “ፍርድ ቤቱ በግድያው በቀጥታ የተሳተፉ አምስት ሰዎች ላይ የሞት ፍርድን ፈርዷል” ብለዋል።

የሳዑዲ ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ የስለላ ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አህመድ አል-አሲሪ የዋሺንግተን ፖስት ጋዜጣ ዘጋቢ በጥቅምት ወር 2018 በሀገሪቱ መንግስት አማካኝነት በቱርክ ኢስታንቡል የተፈጸመውን ግድያ በበላይነት እንደመራና የንጉሣዊው ችሎት ሚዲያ ዛር ሳዑዲ አል-ቃታኒ አማካሪው እንደነበረ ገልጿል።

ሆኖም ቃአታኒ ምርመራ ሲደረግበት ቢቆይም “በቂ ማስረጃ ባለመገኘቱ” ያልተከሰሰ ሲሆን፥ አል ሲሪም ምርመራ ተደርጎበት ቢከሰሰም በተመሳሳይ ምክንያት  ነፃ መሆኑ ተገልጿል።

በቱርክ ኤስታንቡል የሳኡዲ ቆንስላ ጄነራል ሞሃሙድ አልኦታቢም ጥፋተኛ አይደለም በሚል በነፃ እንዲሰናበት ፍርድ ቤቱ ማዘዙም ታውቋል።

በዚህም መሰረት ከጀማል ካሾጊ ግድያ ጋር ታይዞ በቁጥጥር ስር ከዋሉ 11 ተጠርጣሪዎች መካከል 5 የሞት ፍርድ ሲፈረድባቸው፤ ሶስቱቱ የ24 ዓመት እስር ቀሪዎቹ በነፃ እንዲሰናበቱ መደረጉ ነው የተገለፀው።

 

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.