Fana: At a Speed of Life!

የፈረንሳይ ወታደሮች በማሊ ባካሄዱት ዘመቻ 33 ታጣቂዎችን ገደሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፈረንሳይ ወታደሮች በማሊ ባካሄዱት ዘመቻ 33 የታጣቂ ቡድን አባላትን መግደላቸው ተሰማ።

የፈረንሳይ ወታደሮች በማሊ እና ሞሪታኒያ አዋሳኝ ስፍራ ላይ ባሳለፍነው ቅዳሜ በሄሊኮፕተር እና በድሮን በመታገዝ ባካሄዱት ዘመቻ ነው ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለውን የታጣቂዎች ብድን አባላት የገደሉት።

የፈረንሳይ ጦር ባሳለፍነው ዓመት ባካሄደው ዘመቻ የታጣቂ ቡድኑ መሪ አሙዱ ኮፋ ተገድሏል በሚል የተሳሳተ መረጃ ማውጣቷ ይታወሳል።

የፈረንሣይ ጦር አዛዥ ቃል አቀባይ ከዚህ ጋር በተያያዘ በአሁኑ ዘመቻ አሙዱ ኮፋ ኢላማ ስለመሆን አለመሆኑ ለመናገር ፈቃደኛ አልሆኑም።

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በአይቮሪኮስት ዋና ከተማ አቢጃን ለሚኖሩ የፈረንሣይ ማህበረሰብ አባላት  ንግግር ባደረጉበት ወቅት ዘመቻው መካሄዱን ይፋ አድርገዋል።

በዘመቻውም 33 አሸባሪዎች መገደላቸውን፣ አንድ የቡድኑ አባል በቁጥጥር ስር ማዋለቸውን እና በሽበር ቡድኑ አባላት ታግነት የነበሩ ሁለት የማሊ ዜጎችን ነፃ ማውጣት እንደተቻለም ነው ፕሬዚዳንቱ ያስታወቁት።

ዘመቻው የተካሄደው ባለፈው በሄሊኮፕተር መከስከስ 13 የፈረንሳይ ወታደሮች የሚቱበትን ስፍራ ጨምሮ ከአይ ኤስ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የሚጠረጠሩ ታጣቂዎች ይገኙበታል በተባሉ የተለያዩ ስፍራዎች ነው።

ምንጭ፦ ሲጂቲኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.