Fana: At a Speed of Life!

6ኛውን ብሄራዊ ምርጫ በተመለከተ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የውጭ አገራት አምባሳደሮች ገለፃ እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዚህ ዓመት የሚካሄደውን 6ኛውን ብሄራዊ ምርጫ በተመለከተ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የውጭ አገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ገለፃ እየተደረገ ነው።
የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የውጭ ቋንቋና ዲጂታል ሚዲያ ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ማብራሪያውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
                                   
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ተዓማኒና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲካሄድ የተለያዩ ዝግጅቶች ተደርገዋል።
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ተደርጓልም ብለዋል።
ከዚህም ባለፈ የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ለማሳደግ መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ስለመሆኑ ማብራራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያ በ2012 ዓ.ም ልታካሂደው የነበረው ብሄራዊ ምርጫ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት እንዲራዘም መደረጉ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ የጤና ሚኒስቴር የዓለም ጤና ድርጅት ያስቀመጣቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ምርጫ ማካሄድ እንደሚቻል ከተለያዩ አገራት ተመክሮ መውሰዱንም ገልጿል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በጤናሚኒስቴር የቀረበለትን ምክረ ሃሳብ ተቀብሎ ምርጫው እንዲካሄድ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.