Fana: At a Speed of Life!

ወተር ኤይድ የከተሞችን የውሃ አገልግሎት ስርዓት የሚያሻሽል ከ50 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚተገበር ፕሮጀክት በይፋ አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  ወተር ኤይድ ኢትዮጵያ ምእራፍ 2 የከተማ ውሃ ንፅህና እና ስነጽዳት ስርዓት ማጠናከርያ የተሰኘ የከተሞችን የውሃ አገልግሎት የሚያሻሽል ፕሮጀክት በይፋ አስጀመረ።

ፕሮጀክቱ በምእራፍ አንድ ክ2006-2011 ዓ.ም በ20 ክተሞች በተሳካ ሁኔታ ተተግብሮ ክተጠናቀቀው ፕሮጀክት የቀጠለ ሆኖ በመጪዎቹ 5 ዓመታት እንደሚተገበር ይጠበቃል።

የፕሮጀክቱን ወጪ በከፊል የሚሸፍነው በብሪታንያ የሚገኘዉ ዮክ ሻየር ወተር የተባለ የግል ኩባንያ መሆኑምን ወተር ኤይድ ኢትዮጵያ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል።

የወተር ኤይድ ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ያእቆብ መተና፥ ወተር ኤይድ ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ባሉ ክተሞች የውሃ አገልግሎትአሰጣጥን ለማዘመን እየደራ መሆኑን ገልፀዋል።

ድርጅቱ ገንዘብ በማሰሰባሰብና ከአጋሮቹጋር በመሆን  የውሃ፣ ንጽህና እና ሰነ ጽዳት ፕሮግራሞችን በመቅረጽ የከተሞችን የውሃ አገልገሎት አሰጣጥለ ማዘመንና ማህበርስቡን ንጹህውሃ ተጠቃሚ እንደሚሰራም አስታውቋል።

ፕሮጀክቱ በምእራፍ ሁለት በሶስት ክልሎች በሚገኙ 23 ኩታ ገጥም አነስተኛ ከተሞችን የሚመሩ ከተሞች ላይ ከ50 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ በጀት በቀጣይ 5 ዓመታት ይተገበራል።

ፕሮጀክቱ ኩታገጠም አነስተኛ ከተሞችን በአንድ የዞን ዋና ከተማ የማስተባበር አካሄድ የሚከተል ሲሆን፥ በኦሮሚያ፣ በአማራና በትግራይ ክልሎች በመተግበር የውሃ አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን እንደሚሰራም ተገልጿል።

የኮሮናን ቫይረስ ስርጭት ታሳቢ በማድረግ በኢንተርኔት በተካሄደው የፕሮጀክቱን በይፋ የማስጀመር መርሃ ብግር ላይ ከውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስቴር፣ ከጤና ጥበቃ ሚንስቴር፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማትና ከክልል የውሃ ቢሮ እንዲሁም ከወተር ኤይድ ዩኬና ከምስራቅ አፍሪካ ወተር ኤይድ ማስተባበርያ ጽህፈት ቤት ተወካዮች ታድመውበታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.