አቶ ልደቱ አያሌው 100 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው እንዲወጡ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፈቀደ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ልደቱ አያሌው 100 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው እንዲወጡ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፈቀደ።
አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት በጦር መሳሪያ አስተዳደር አዋጅ 1177/ 2012 በመተላለፍ ላይ ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ መርምሮ ነው ፍርድ ቤቱ ዋስትና የፈቀደው።
ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ አያሌው የተከሰሱበትን ጉዳይ ለመመልከትም መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም ፍርድ ቤት አንዲቀርቡም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በታሪክ አዱኛ