Fana: At a Speed of Life!

በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ሊገባ የነበረ ባለቤቱ ያልታወቀ 300 ኩንታል ቀይ ሽንኩርት ተያዘ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህገ ወጥ መንገድወደ ሀገር ሊገባ የነበረ ባለቤቱ ያልታወቀ 300 ኩንታል ቀይ ሽንኩርት መያዙን በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የመተማ ዮሐንስ መቅረጫ ጣቢያ አስታውቋል፡፡
 
ሽንኩርቱ የተያዘውም በተሳቢ አይ ቬኮ ትራከር በሱዳን- ገላባት በኩል ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ሲሞክር በጣቢያው ሰራተኞች በተደረገ ፍተሻ ነው ተብሏል፡፡
 
ህገ ወጥ ሽንኩርቱ ባለቤት የሌለው እና የጉምሩክ ስነ-ስርዓት ያልተፈፀምበት መሆኑንም የመተማ ዮሐንስ መቅረጫ ጣቢያ አስተባባሪ ምክትል ኮማንደር መስቀሌ አርጋው ተናግረዋል፡፡
 
የህገ ወጥ ሽኩርቱን የአስመጪ እና የመኪናውን ባለቤት ለማወቅም ፖሊስ አስፈላጊው ምርመራ እያደረገ መሆኑን ነው አስተባባሪው የገለጹት ፡፡
 
የመተማ ዮሐንስ ከተማ የድንበር ከተማ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ በሱዳን-ገላባት በርካታ የገቢና ወጭ ዕቃ እንቅስቃሴ እንደሚደረግ ያነሱት ምክትል ኮማንደር መስቀሌ፣ ህብረተሰቡ መሰል ህገ ወጥ ድርጊቶችን ሲመለከት ለሚመለከተው አካል ጥቆማ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.