የህሙማን ደህንነት ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ2ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 7 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህሙማን ደህንነት ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ2ኛ ጊዜ እየተከበረ መሆኑ ተገልጿል።
ቀኑም ”የጤና አገልግሎት ሰጭዎች ደህንነት፣ ለህሙማን ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ መሆኑ ተገልጿል።
በኢትዮጵያም የህሙማን ደህንነትቀን እየተከበረ ሲሆን÷ በቅድሚያ በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የኮቪድ 19 ቫይረስ የተገኘባቸው ታካሚ የጤና ባለሙያዎችን በማመስገን ተጀምሯል።
በስነስርዓቱ ላይ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ ÷የህሙማንን ደህንነት ለመጠበቅ የጤና ባለሙያዎች ደህንነት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ አሳይቷል ብለዋል።
አያይዘውም በኢትዮጵያ 1 ሺህ 400 ያህል ጤና ባለሙያዎች በቫይረሱ መያዛቸውንና የ2 ባለሙያዎች ህይወትም ማለፉን ገልጸዋል።
በመሆኑም ቀኑን ከማክበር ባለፈ ሁሉም ባድርሻ አካላት ተገቢው ስራ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በበአሉ ማጠናቀቂያ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሚገኙበት በሚሊኒየም አዳራሽ የህክምና ጣቢያ የጧፍ ማብራትና የማጠቃለያ የምስጋና ስነስርዓት እንደሚካሄድ ከጤና ሚኒስቴር ያገኘኘው መረጃ ያመለክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።