Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከ1 ሚሊየን በላይ ሰዎች የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲደረግ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከ1 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የኮቪድ-19 የላቦራቶሪ ምርመራ እንዲደረግ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ።

በኢትዮጵያ እስከ ትናንት ድረስ 1 ሚሊየን 18 ሺህ 847 ሰዎች የኮቪድ 19 የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

ይህንን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ፥ “የኮቪድ19ን የምርመራ መጠን ከፍ ለማድረግ እና የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት የሚያስችል ብሔራዊ መረጃን ለማግኘት ለ1 ወር የሚዘልቅ ሀገር አቀፍ ዘመቻ ማካሄዳችን ይታወሳል” ብለዋል።

በዚህም “ከ1 ሚሊየን የሚበልጡ ሰዎች በዘመቻው ለመመርመር እንዲችሉ ያደረጉትን ሁሉ አመሰግናለሁ” ሲሉም ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አክለምው፥ “መላው ኢትዮጵያውያን መጪውን አዲስ
ዓመት ስንቀበል የጥንቃቄ ርምጃዎችን መተግበራችንን በርትተን እንድንቀጥልም አሳስባለሁ” ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል።

በ2013 የበለጠ ይጠበቅብናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ፥ ጤናችንን በመጠበቅ ፈተናውን በአሸናፊነት እንወጣ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.