Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ የትምህርት አጋርነት በኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓቱን ለመደገፍ 15 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዓለም አቀፉ የትምህርት አጋርነት ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓቱን ለመደገፍ 14 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አደረገ።

በዓለም አቀፉ የትምህርት አጋርነት የተደረገው ድጋፍ የኮሮና ቫይረስ በትምህር ስርዓቱ ላይ ላስከተለው ችግር ምላሽ ለመስጠት መሆኑን ከዓለም ባንክ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ድጋፉ ትምህርት ቤቶች ዝግ ሆነው በሚቆዩበት ጊዜ ተማሪዎች ትምህርታቸውን መከታተል እንዲችሉ፣ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ትምህርት ቤቶቹ እንዲከፈቱ ለማስቻል እና የትምህርት ስርዓቱን ከችግሮች በፍጥነት መውጣት እንዲቻል ለመደገፍ የሚውል ነው ተብሏል።

በዚህ ድጋፍ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ትምህርት ቤቶቹ እንዲከፈቱ በሺዎች ለሚቆጠሩ ተማሪዎች ሳኒታይዘር እና የደህንነት መጠበቂያ ቁሳቁሶች እንደሚቀርቡ ተገለጿል።

እንዲሁም ለተማሪዎች እና ለተማሪ ወላጆች በተለያዩ ጉዳዮች ግንዛቤ ለመፍጠር እና በቴክኖሎጂ በመታገዝ የርቀት ትምህርት ለመስጠት ድጋፉ እንደሚደረግ ተጠቁሟል።

የገንዘብ ድጋፉ በዓለም ባንክ በኩል ለኢትዮጵያ ተደራሽ እደሚሆንም ተነግሯል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.