Fana: At a Speed of Life!

ጃፓናዊቷ ጋዜጠኛ በአስገድዶ መደፈር በደረሰባት ጥቃት በፍርድ ቤት በማሸነፍ የ30 ሺህ ዶላር ካሳ አገኘች

ሺዮሪ ኢቶ የተባለችው  ጃፓናዊት ጋዜጠኛ በፈረንጆቹ በ2015 ላይ ራሷን በሳተችበት ወቅት ነበር ኒሪዮኪ ያማጉቺ  በተባለ ግለሰብ  ተገዳ የተደፈረችው ።

ድርጊቱን ተከትሎም ኢቶ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ  ስትከራከር መቆየቷ በዘገባው ተመላክቷል።

ይሁን  እንጂ  ጉዳዩን  የሚከታተለው ዓቃኔ ህግ የተጠርጣሪውን ወልጀለኛነት የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች የሉም በሚል ክሱን ውድቅ ያደርግባታል።

ይህን ተከትሎም  ሺዮሪ ኢቶ ጉዳዩን ወደ ሲቪል ፍርድ ቤት በመውሰድ በድጋሜ መከታተል ትጀምራለች።

ከዚህ ባለፈም አብዛኞቹ የአስገድዶ መደፈር  ወንጀልን ሲደርስባቸው ሪፖርት  በማያደርጉባት  ጃፓን ጉዳዩን አደባባይ በማውጣት የተለያዩ ዘመቻወችን  ማካሄዶ ተገልጿል።

በዚህም “እኔም” በተሰኘው እና  በሀገሪቱ የሚፈጸመውን ተመሳሳይ ወንጀል በሚያወግዘው  እንቅስቃሴ ላይ ምሳሌ እስከመሆን ደርሳለች።

ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የጃፓኑ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ጉዳይ በመመልከት በአስገድዶ መደፈር ወንጀል ተጠቂ ለሆነቸው ለጋዜጠኛ የ3 ነጥብ 3 ሚሊየን የን ወይም የ30 ሺህ ዶላር ካሳ እንዲከፈላት ትዕዛዝ አስተላለፏል።

ውሳኔው ይፋ ከተደረገ በኋላ “በጣም ደስተኛ ነኝ” ያለቸው የ 30 ዓመቷ ኢቶ ፥“ድል” የሚል ምልክትን የያዘ ጸሁፍ አስነብባለች፡፡

 

ምንጭ፣ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.