Fana: At a Speed of Life!

የአዶኒስ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደራሲ አድነው ወንድይራድ ወይንም አዶኒስ የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡

አዶኒስ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በዕሁድ መዝናኛ ፕሮግራም የተላለፉት የገመና እና መለከት ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎች ደራሲ ነበር፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ህንጻ ንድፍ ያጠናው አዶኒስ ከቴሌቪዥን ተከታታይ ድራማዎች በተጨማሪ የአና ማስታወሻን በመተርጎም ለንባብ አብቅቷል፡፡

እንዲሁም የአዶልፍ ሔክማን መጽሐፍ ተርጓሚ፣ የፕሮፌሰሩ መጽሐፍ ፣ የሕጻናት መዝሙሮች እና የበርካታ ፊልሞች፣ የኪነ ጥበብ ሥራዎች ደራሲ እና ተርጓሚ ነበር።

ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት የነበረው አዶኒስ ትውልዱ አዳማ ከተማ ነበር፡፡

ወዳጆቹ በባህሪው ብዙም ወደ መገናኛ ብዙኀን የመቅረብ እና የመታየት ፍላጎት እንዳልነበረው ይናገራሉ፡፡

አዶኒስ በኒሞንያ ህመም ምክንያት በምኒልክ ሆስፒታል ህክምና ሲከታተል ቆይቶ በትናትናው ዕለት በ57 ዓመቱ ህይወቱ አልፏል፡፡

በቅድስት ወልዴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.