Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱዳንን ሊጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ በቀጣዩ ሳምንት በሱዳን ጉብኝት ሊያደርጉ ነው፡፡
 
ጉብኝቱ ሃገራቱ ግንኙነታቸውን ለማደስ እና የሃገሪቱን የሽግግር መንግስት መደገፍ በሚቻልበት አግባብ ላይ ለመምከር ያለመ ነው ተብሏል፡፡
 
በጉብኝታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ እና ከሱዳን የሽግግር መንግስት ሉአላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ጋር ይመክራሉ፡፡
 
በምክክራቸውም አሜሪካ ለሱዳን የሽግግር መንግስት ድጋፍ ማድረግና ማገዝ በምትችልበት መንገድ ላይ እንደሚወያዩም ይጠበቃል፡፡
 
ፖምፒዮ ከእስራኤል መልስ ያደርጉታል የተባለው ጉብኝት በሃገራቱ ግንኙነት ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ተብሎም ነው የሚጠበቀው፡፡
 
ሱዳን በአሜሪካ ሽብርተኝነትን በመደገፍ በጥቁር መዝገብ ውስጥ የሰፈረች ሲሆን ይህም የብድርና እና እዳ ቅነሳ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ በምታደርገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሮባታል፡፡
 
ምንጭ፡-ቢቢሲ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.