ኬንዶን በመጠቀም በ1 ደቂቃ ውስጥ 20 ክብሪቶችን የለኮሰው ግለሰብ የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት ሆኗል
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የማርሻል አርቱ ባለሙያ ኬንዶን ብቻ በመጠቀም በአንድ ደቂቃ ውስጥ 20 ክብሪቶችን መለኮስ መቻሉ ተሰምቷል።
ቻይናዊው የማርሻል አርት ባለሙያ በአንድ ደቂቃ ውስጥ ብቻ ኬንዶን ወይም ኑንቻኩን አወዛውዞ በመጠቀም 20 የክብሪት ፍሬዎችን በማብራት የዓለም የድንቃድንቅ እና ክብረ ወሰኖች መዝገብ ላይ ስሙን ማስፈር ችሏል።
ባለሙያው ፈጣን የእጅ እንቅስቃሴ እድገት እንዲኖር እና አቋምን የማሻሻል የሚረዳውን እና በማርሻል አርት ዘርፍ ለሥልጠና ጥቅም ላይ የሚውለውን መሣሪያ በመጠቀም ብቻ ይህን መከወኑም ብዙዎችን አስገርሟል።
የ28 ዓመቱ የማርሻል አርት ባለሙያ አሁን የደረሰው ውጤት ላይ ለመድረስም 10 ዓመት እንደፈጀበት ተናግሯል።
ቻይናዊው ወጣት በፈረንጆቹ በ2009 ይህንኑ መሳሪያ እያወዛወዘ በመጠቀም 70 የበሩ ሻማዎችን በ60 ሰከንድ በማጥፋት ስሙን በዚሁ መዝገብ ላይ ማስፈር ችሏል።
በማርሻል አርት ዘርፍ በአለም በርካታ ውድድሮችንም ማሸነፍ የቻለው ወጣቱ አሁን በሻንጋይ ትምህር ቤቶች እውቀቱን እያጋራ መሆኑም ተነግሯል።
ምንጭ፡-upi.com