Fana: At a Speed of Life!

961 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 961 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት በተደረገ 3 ዙር በረራ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በዚህም 578 ወንዶች፣ 336 ሴቶች እና 47 ጨቅላ ህፃናት ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ሲሆን፤ ከተመላሾች መካከል 48 እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

በ4ኛው ዙር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 50 ሺህ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ዕቅድ ከመጋቢት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ መጀመሩ ይታወቃል፤ በዚህም እስካሁን 1 ሺህ 961 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

በተያያዘ ዜና በሳምንቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከኦማን 168 ወንዶች ከሊባኖስ ደግሞ 20 ሴቶችና 1 ጨቅላ ህፃን በድምሩ 189 ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.