Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 27 የትራፊክ መብራት መጋጠሚያዎች ላይ የሶላር ሃይል መቀበያ መሳሪያ ተተከለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን 27 የትራፊክ መብራት ባሉባቸው ቦታዎች ላይ የሶላር ሃይል መቀበያ መሳሪያ መትከሉን ገለጸ።

ቀደም ሲል በኤሌክትሪክ መቆራረጥ ሳቢያ የትራፊክ መብራቶች ያለመስራት ችግር ያጋጥማቸው እንደነበር አስታውሶ፤ ችግሩን ለመፍታት የትራፊክ እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው ቦታዎች በፀሐይ ሃይል የሚሰራ አቅርቦት እንዲኖር መደረጉ ጠቁሟል፡፡

በዚህም በጀርመን አደባባይ፣ ጀሞ ሚካኤል፣ አየር ጤና፣ 18 ማዞሪያ፣ 3 ቁጥር ማዞሪያ፣ ጦርሃይሎች፣ ለገሀር፣ እስጢፋኖስ፣ ቅዱስ ዮሴፍ፣ ብሄራዊ ቴአትር፣ ፖስታ ቤት፣ ጥቁር አንበሳ እና ሰንጋተራ የሶላር ሃይል መቀበያ መሳሪያው ተተክሏል።

እንዲሁም ባንኮዲሮማ፣ ፓርላማ፣ አትላስ፣ ቦሌ ሚካኤል፣ አፍሪካ ህብረት፣ ትምባሆ፣ ሾላ ገበያ፣ ሾላ ፔፕሲ፣ ሳህሊተማርያም፣ ቦሌ ሚሊኒየም እና ቦሌ ሱፐር ማርኬት መሳሪያው መተከሉ ተገልጿል፡፡
በአሁኑ ወቅት በመዲናዋ 90 ቦታዎች ላይ የትራፊክ መብራት እንዳለና የትራፊክ ፍሰቱም ሰላማዊ እየሆነ መምጣቱን የባለስልጣኑ መረጃ ጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.