Fana: At a Speed of Life!

ከጣሊያን ጋር የተፈረመውን የክህሎት መሰረተ ልማት ግንባታ ስምምነት ለመተግበር የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያና ጣሊያን መንግስት መካከል የተፈረመውን የክህሎት መሰረተ ልማት ግንባታ ስምምነት ወደ ትግበራ ለማስገባት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ።

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ ስምምነቱን ወደ ትግበራ ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከጣሊያን መንግስት ልዑካን ቡድን ጋር ውጤታማ ውይይት አካሂደናል ብለዋል።

በውይይቱ የክህሎት መር ሥራ ዕድል ፈጠራ እና የክህሎት መሰረተ ልማት ግንባታ ስምምነት በፍጥነት ወደ ትግበራ የሚሸጋገርበትን ሁኔታ በዝርዝር ተመልክተን ቀጣይ አቅጣጫዎች አስቀምጠናል ሲሉ ገልጸዋል።

ስምምነቱ በሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ልማት ዘርፍ በርካታ ሴቶችንና ወጣቶችን የሙያ ባለቤት በማድረግ ወደ ሥራ ማስገባት የሚያስችል መሆኑን አመልክተዋል።

በተጨማሪም በአፍሪካ በአይነቱ ልዩ የሆነውን የክህሎት ፓርክ በመገንባት ኢትዮጵያ ለያዘችው ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዞ አይነተኛ ሚና ይጫወታል በማለት ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የጣሊያን ኤምባሲን ጨምሮ ስምምነቱ ወደ ተግባር እንዲሸጋገር ጥረት እያደረጉ ለሚገኙ አካላት ሚኒስትሯ ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.