በፈንታሌ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ነዋሪዎችን ስጋት ላይ መጣሉ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በፈንታሌ ተራራ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችን ስጋት ላይ መጣሉ ተነግሯል፡፡
የፈንታሌ ወረዳ ኮሙኒኬሽን እንዳለው፤ የመሬት መንቀጥቀጡ እስካሁን የከፋ ጉዳት ባያደርስም ነዋሪዎችን ስጋት ላይ ጥሏል።
በዚህም የአካባቢው ነዋሪዎች ቀያቸውን ለቀው ለመሸሽ እየተገደዱ እንደሆነ ገልጿል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጡ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ ሲሆን ትናንት ምሽት ላይ በፈንታሌ ተራራ አካባቢ ፍንዳታዎች ተከስተዋል ሲልም የወረዳው ማስታወቂያ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
በአካባቢው እስከ 5 ነጥብ 3 የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑ ይታወቃል።
በይስማው አደራው እና ሰሎሞን ይታየው