Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ከ266 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ዉሃ ተጠቃሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ከ266 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ዉሃ ተጠቃሚ መሆናቸውን የክልሉ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ ፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ዉሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አክሊሉ አዳኝ (ኢ/ር) የቢሮው ስራ አፈጻጸም በተገመገመበት ወቅት እንዳሉት÷ በግማሽ ዓመቱ 83 የመጠጥ ዉሃ ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናቀዋል።

በዚህም ከ266 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አብራርተዋል።

በማዕድንና ኢነርጂ ዘርፍም ለ13 ሺህ 935 ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል የተፈጠረላቸው መሆኑም በሪፖርቱ መገለጹን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

በተጨማሪም ባለፉት 6 ወራት ከ490 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች የተሻሻሉ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎችንና የሶላር ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉም ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.