Fana: At a Speed of Life!

የኖርዌይ ባለሃብቶች መዋዕለ ነዋያቸውን በኢትዮጵያ እንዲያፈሱ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኖርዌይ ባለሃብቶች መዋዕለ ነዋያቸውን በኢትዮጵያ እንዲያፈሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ጥሪ አቅርበዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኖርዌይ ፍትህ ሚስትር ኤምሊ ኧንገር መኸል ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በውይይቱ ላይ እንዳሉት ፥ ኖርዌይ የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ አጋር ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ ናት።

የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት አሁን ካለበት ደረጃ ይበልጥ ለማጠናከር ኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ አመላክቷል።

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በመተግበር ላይ የምትገኘው የኢኮኖሚ ሪፎርም ለውጭ ኩባንያዎች የተሻለ የተሳትፎ ዕድልን የፈጠረ በመሆኑ የኖርዌይ ባለሃብቶች መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱም ጠይቀዋል።

የኖርዌይ ፍትህ ሚኒሰትር ኤምሊ ኧንገር መኸል በበኩላቸው ፥ ኖርዌይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.