Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው ከ456 ሺህ ቶን በላይ ደረቅ ቆሻሻ አስወገደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ከመዲናዋ ተሰብስቦ የቀረበለትን 456 ሺህ 898 ቶን ቆሻሻ ማስወገዱን የአዲስ አበባ ከተማ ጽዳት አሥተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ከዚህ ውስጥ 109 ሺህ 608 ቶን ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫነት መዋሉን በኤጀንሲው የረጲ የላንድፊል አሥተዳደር ዳይሬክተር ነብዩ ተስፋዬ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም 374 ሺህ 290 ቶን ደግሞ በላንድፊል እንዲወገድ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡

በተጠናቀቀው ሥድስት ወር ከቀረበ አጠቃላይ ደረቅ ቆሻሻ 76 በመቶው በላንድፊል መወገዱን እና 24 በመቶው ለኃይል ማመንጫነት መዋሉን አብራርተዋል፡፡

በቀን በአማካይ 607 ቶን ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫነት እንዲሁም 1 ሺህ 942 ቶን ደግሞ በላንድፊል የተወገደ ቆሻሻ እንደቀረበም ተናግረዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.