Fana: At a Speed of Life!

በኬኒያ አውሮፕላን ተከስክሶ የ3 ሰዎች ሕይዎት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኬኒያ ማሊንዲ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በምትገኘው ክዋቾቻ ከተማ በደረሰ የአነስተኛ አውሮፕላን አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይዎት ማለፉ ተሰምቷል፡፡

የዐይን እማኞች አውሮፕላኑ በአካባቢው የነበሩ ሰዎችን መምታቱንና ከዚያም በእሳት መያያዙን ገልጸዋል፡፡

ሁለት ሰዎች በአውሮፕላኑ ስብርባሪዎች ተመትተው ወዲያውኑ ሕይዎታቸው ሲያልፍ፥ አንዱ በእሳት ከባድ ጉዳት ከደረሰበት በኋላ መሞቱን የአካባቢውን ባለስልጣናት ዋቢ አድርጎ አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡

በሌላ በኩል በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ አንድ ፓይለት እና ሁለት ተማሪዎች አደጋው ከመድረሱ በፊት መውጣታቸውን እና አሁን ላይ የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን የዘገበው ደግሞ አሶሺየትድ ፕሬስ ነው፡፡

ሰሞኑን በተለያዩ የዓለም ሀገራት በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የአውሮፕላን አደጋ የአቪየሽን ዘርፉን እየፈተነው ነው ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.