Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል የሱልጣን አሊሚራህ ሀንፈሬ ቤተ-መንግሥት ዕድሣት እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ ገንዘብ በአፋር ክልል አይሳኢታ ከተማ የሚገኘው የሱልጣን አሊሚራህ ሀንፈሬ ጥንታዊ ቤተ-መንግሥት እየታደሠ ነው፡፡

ለእድሣቱ ከሚያስፈልገው 174 ሚሊየን 585 ሺህ 826 ብር እስከ አሁን 134 ሚሊየን 804 ሺህ 391 ብር ከመጽሐፉ ሽያጭ መሰብሰቡን የአፋር ክልል ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቤተ-መንግሥቱን የማስዋብ፣ ማደሥና ማስፋፋት ሥራው አጠቃላይ አፈጻጸምም 67 ነጥብ 41 በመቶ መድረሱን ነው የቢሮው ምክትል ኃላፊ አብዱ መሐመድ ለፋና ዲጂታል ያረጋገጡት፡፡

ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ ወደ ሥራ መገባቱንም አውስተዋል፡፡

የመጽሐፉ ሽያጭ ገቢ ጥንታዊ ቤተ-መንግሥቱን ለማስዋብ፣ ለማደሥ እና የማስፋፊያ ሥራ ለማከናወን የሚውል መሆኑን በመገንዘብ የክልሉ ሕዝብ፣ ባለሃብቶች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በግዥው ላይ በንቃት እንዲሳተፉ የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

የማስፋፊያ ሥራውን እስከ ቀጣይ ዓመት መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑንም ነው ያስረዱት፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.