Fana: At a Speed of Life!

የሀገራዊ ፕሮጀክቶች በክልሎች ደረጃ ያለ አፈፃፀም ግምገማን  ተከትሎ ስብሰባ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገራዊ ፕሮጀክቶች በክልሎች ደረጃ ያለ አፈፃፀም ግምገማን ተከትሎ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ  የተመራ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ ተካሂዷል።

 

በሚኒስትሮች ምክር ቤት የሀገራዊ ፕሮጀክቶች በክልሎች ደረጃ ያለ አፈፃፀም ግምገማ ተደርጎ እንደነበር ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት  ያገኘነው መረጃ አስታውሷል።

 

ይህን ተከትሎ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ  የተመራ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ ተካሂዷል።

 

በስብሰባው የመስክ ምልከታና ግምገማ ቡድኖች መሪዎች ግምገማዎቻቸውን እና ግኝቶቻቸውን ማቅረባቸው ተገልጿል፡፡

 

ይህ የሱፐርቪዥን እና የግብረመልስ ሂደት ሰፋ ያለው ሥርዓትን የማጠናከር ተግባር አካል መሆኑ እና አፈፃፀሞችን  በዞን እና ወረዳ ደረጃ በመመልከት ክፍተቶችን መለየትን አላማ ማድረጉ ተመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.